Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
ምስጋናዬ ምስጋናዬ ይሁን ላንተ ጌታዬ
በዙፋንህ ላለኸው እጅግ ለከበርከው
ሁሉም የሚያመልኩህ በሰማይ ላለከው
እኔም እበዛለሁ እጨምራለሁ
አዲስ ምስጋና አዲስ ክብር
ይብዛለት እንጂ ለእግዚአብሔር
ያልተለመደ አዲሱን ቅኔ
እስቲ አምጡለት ለዚህ ጌታዬ (X2)
ከኛ ጋር ሆናችሁ አመስግኑ
የሚገባውን ክብር ስጡት
ስለ ወደደን አድኖናል (X2)
ክብርን ልንሰጠው ይገባናል (X2)
ፍጥረት ይሰብሰብ ጌታን ሊያመልክ
ሁሉም ዝቅ ይበል በዙፋኑ ስር
በተዋበ ቃል ባማረ ዜማ
እናመልካለን ዛሬ እንደገና
አልተገኘም ከቶ አንተን የሚመስልህ
የማትለወጥ ጌታ እየሱስ
ዛሬም ይወራ ጌታ ስራህ
ሁሉም ይናገር ታላቅነትህን (X2)