Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
እግዚአብሔር ኃይሉ ከፍ ያለውን ነገር ያደርጋል
ለጌታ ለኢየሱስ ምንስ ይሳነዋል
ሁሉ ይቻላል (X4)
ደመናውም ባይኖር ንፋስም ባይነፍስ
አምላኬ ታማኝ ነው
በባዶ ነገር ላይ በሙላት መገለጥ
ጌታ ልማዱ ነው
በዘመናት መሃል ድንቅን የሚሰራ
እየሱስ ጌታ ነው
ስንፍና አላወራም በዚህ ታላቅ ጌታ እተማመናለሁ
አይችልም አልልም አምላኬን (X2)
አይችልም አልልም ጌታዬን
በሁኔታዎች አምላኬን ገድቤ
እንዲህ ነው አልልም
በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ግራ ተጋብቼ
ግራ ቀኝ አይደለም
በምድረ በዳ ላይ ደግፎ ማቆምን እሱ ያውቅበታል
ከማንም ከምንም ጌታ ይመቸኛል
ይመቻል አምላኬ (X2)
ይደላል ጌታዬ ጌታዬ
እግዚአብሔር ሲነሳ ማነው ተው የሚለው
ሁሉንም ይሠራል
ጌታ ኤልሻዳይ ነው ታሪክን ገልብጦ
ያሻውን ያደርጋል
ቢያፈርስ ቢተክል ሚቃወመው ማን ነው
ስልጣን በእጁ ነው
ሁሉንም የሚያከናውነው እግዚአብሔር ትልቅ ነው
እግዚአብሔር ይችላል ሁሉንም(X2)
እግዚአብሔር ያደርጋል ሁሉንም