Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
እግዚአብሔር ሆይ በምህረትህ ምራኝ (X3)
ዘመኔን ልጨርስ አንተ እየመራኸኝ (X3)
አለምን እያየው ልቤ አያድላህ
በዚሁ እንዳልጠፋ ጠብቀኝ አባባ (X3)
ብዙ ስራ እያለ በእኔ የሚሰራ
ዛሬ በማየቴ እንዳልቀር አደራ (X4)
ሙሽራው ኢየሱስ በክብር ስትመጣ (X3)
ዘይቴን ጨርሼ እኔ እንዳልታጣ (X3)
ባንኳኳ ብለፋ ማን ይከፍትልኛል
በቤትህ መኖሬ ለእኔ ይሻለኛል (X4)
ውቢቷ ሀገሬ እየሩሳሌምን (X3)
ሰላምና እረፍት ደስታ የሞላባትን (X3)
ለማይጠቅመው ለዚህ አለም ብዬ
ላጣ አልፈልግም ሀገሬን እርስቴን (X4)