Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
ሀገራችን ነው በሰማይ
እንሄዳለን ጌታችን ልናይ
አይደለም ተስፋችን ምድራዊ
ታይቶ የሚጠፋ ጊዜያዊ
በሰማይ ለኛ እቤት አለን
ርስታችንን ልንወስን እንሄዳለን
ጌታችንን ልናይ እንሄዳለን
የሰው አይን ያላየው
የሰው ጆሮ ያልሰማው
ጌታችን ለኛ ያዘጋጀልን
የከበረ ቤት በሰማይ አለን
ልንኖር በሰላም በደስታ
ልናገኝ ለነብሳችን እርካታ
እንሄዳለን ሀገር በሰማይ አለን
አክሊላችንን እንወርሳለን
ዋልታ ለቅሶ የሌለበት
በጉ እንባችንን የሚያብስበት
ከመላእክት ጋር በአንድነት
ንጉሡን ከፍ የምናደርግበት
ሀገር አለን በሰማይ
ዘላለማዊ እረፍት የሞላበት
እራብ ርዕሳት የማይሰማበት
ሀገር አለን በሰማይ