Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
ጌታ የረዳው ሰው ምንኛ የታደለ ነው (X2)
ቀኝ እጁን በእጁ የያዘው
የሰው ምንኛ የታደለ ነው
አምላኩ የሆነው
ተማምኖ ይኖራል ከእርሱ የተነሣ
ስጋት አይገባውም በአንዳች ነገር
የእርሱ ስለሆነ ጌታ እግዚአብሔር
እግዚአብሔር ኃያል በስራው ጻዲቅ
አሰራሩ ትልቅ እጅግ የሚያስደንቅ
አላየልኝ ብሎ ተስፋ ለቆረጠው
ፈጥኖ የሚደርስለት ጌታ እየሱስ ነው
እግዚአብሔርን ብሎ አረ ማን ወደቀ
እሱን ይዞ ወጥቶ የትኛው ከሰረ
ሰምቶ እንዳልሰማ እንደ አዛብ አምላክ
አይደለም አምላኬ የእኔ እግዚአብሔር
ጌታን የታመነ እርሱን የተጠጋ
ዘመኑን በሙሉ ይኖራል በተድላ
አቤት ስንቱ አረፈ እርሱን የታመነ
ሂወቱ በሙሉ በጌታ የተያዘ