Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
ያልፋል ሁሉ ያልፋል
ያልፋል ይህም ያልፋል
ያልፋል ያም ያልፋል
እየሱስ ግን ቋሚ ገንዘቤ ነው
እየሱስ ግን ቋሚ ንብረቴ ነው
በምድር ላይ ዛሬ የምናየው
አንዳች የለም ከእኛ የሚቆየው
ሁሉም አላፊ ጠፊ ነው
እየሱስ ዘላቂ ሀብት ነው
በዓለም ላይ ቋሚ ነገር የለም
ዛሬ ታይቶ ለነገ አይቆይም
ብርም ቢሆን ወርቅ ኃላፊ ነው
አንዱ ጌታ ዘላለማዊ ነው
መልክና ውበት እንደ ጠዋት ጤዛ ነው
በአንድ ማግስት እኛን የሚከዳው
እውቀትና ጥበብም ከንቱ ነው
ሰማይ ምድር ሁሉ አላፊ ነው