Tumim Song 78
የትላንቱ ዛሬ ተረስቷል




የትላንቱ ዛሬ ተረስቷል

Style = ----
‎Temp = ----
‎Tran = ----
‎Scale = ----
‎Cord = ----
>>>>>>

0:00
0:00



የትላንቱ ዛሬ ተረስቷል
ነገሬ ውብ ሆኗል
የትላንቱ ዛሬ ተነስቷል
መቅበዝበዜ ቀርቷል

ትላንት ማን ነበርኩኝ እኔ አውቃለሁ
አንተ ስትረዳኝ ሰው ሆኛለሁ
ሌላ ምን እላለሁ ቃላት የለኝም
ክበርልኝ ጌታ ክበርልኝ

ማበል ተነስቶ ሲያናውጠኝ
ጠላቴ ሲያጓራ እኔን ሊውጠኝ
ውዴ ከተፍ ብለህ ሰው አረከኝ
ውርደቴን በክብር ለወጥክልኝ (X2)

ማንም በሌለበት ለኔ ደርሰህ
ማንም ሳያዝንልኝ አንተ አሰብከኝ
ለውለታ ጌታ ምን ልክፈልህ
ከእግር ስር ሆኜ ልስገድልህ (X2)

ከማንም በላይ ወድሃለው
አንተ ስላለኸኝ ከብሪያለሁ
መቅበዝበዜ ቀርቶ አርፍያለው
ሰላም እና እረፍት አግኝቻለሁ (X2)

View Favorites