Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
አንተ ሞቴን የሞትክልኝ
አንተ ህይወት የሰጠኸኝ
አንተ ነህ ጌታዬ እኔን ሰው ያረከኝ
ከትቢያ አንስተ በቤትህ የሾምከኝ (X2)
በእኔ ፋንታ ሞተህ ህይወት የሰጠኸኝ
ከውርደት አንስተ ጌታ ያከበርከኝ
ከብሬአለሁ እኔስ አሁንስ በቤትህ
ከእግር ስር ወደቄ ጌታ ላመስግንህ
በቀራኒዮ ሞተ በደምህ የገዛኸኝ
ከሃጥያት ባርነት ነጻ ያወጣሀኸኝ
ይሄ ሲያስደንቀኝ ክብርህን ጨመርክልኝ
ባሪያ አልልም የእኔ ልጅ ነህ አልከኝ
ኃጢአቴን አጠብከው ጌታዬ በደምህ
የሞትን መጋረጃ ገፈከው በሃይልህ
ከአንተ ጋር አለሁ አርነት ወጥቼ
አከብርሃለሁ እጆቼን አንስቼ