Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
አምላኬ ንጉሴ ከፍ አደርግሀለሁ
ስምን ለዘላለም እባርካለሁ
በድቅድቅ ጨለማ ባስፈሪው ለሊት
ጠላቴን አዋርደህ ክብርን ሰጥተኸኛል
ያስለቀሰኝ ዛሬ ሽንፈት ደርሶበታል
በክንድህ ያስደገፍከኝ ጌታዬ አንተ ነህ
ለክብርህ ወደር የለው ክብር ይሁንልህ
ምን ብዬ ልናገር ያደረክልኝን
ሳደንቅህ ኖራለሁ እየሱሴ ስራህን
ቃላቶች ያጥሩኛል ጌታህ ለውለታህ
ምስጋና ነው ያለኝ አምላኬ ላክብርህ
ነፍሴን ከአዳኝ ወጥመድ ጌታ አዳንከኝ
ከሚያስደነግጠኝ የሱሴ ታደከኝ
ታዲያ ለዚህ ጌታ ምን እከፍለዋለሁ
ምጋናን ዘወትር በፊትህ አቀርባለሁ