Tumim Song 68
አምላኬ አንተ መታመኛዬ




አምላኬ አንተ መታመኛዬ

Style = ----
‎Temp = ----
‎Tran = ----
‎Scale = ----
‎Cord = ----
>>>>>>

0:00
0:00



አምላኬ አንተ መታመኛዬ
ወዳጅም አንተ ነህ ፅኑ ጉኣደኛዬ
ብርቱ ጠበቃዬ መልካም እረኛዬ
እየሱስ አንተ ነህ የኔ መከታዬ

እየሱስ አንተ ነህ ጌታዬ ንጉሴ
የህይወቴ አለቃ ጠበቃና ዋሴ
ስለዚህ ሳልፈራ ካንተ ጋር ኖራለሁ
በክንፎቹ ጥላ እኔ እጋረዳለሁ

ንጉሴ አንተ ነህ ሁሌ መከታዬ
የዘላለም አባት የኔ መኖርያዬ
የሰላሜ ገዢ የሆንክልኝ አሌንታዬ
ባንተ እደገፋለሁ ሆነህ ማረፍያዬ

ጌታዬ በቤትህ ለዘላለም ኖራለሁ
እንዳንተ የሚሆን ከየት አገኛለሁ
አቤቱ አምላኬ አመሰግናለሁ
ካንተ የተነሳ እዚ ደርሻለሁ

ምን ልበል እኔ ለዚህ ውለታህ
አንተ እኮ ልዩ ነህ ማንም አይመስልህ
ከምስጋና ሌላ ስለሌለኝ
ለዘላለም ተባረክ ሁሌም እልሀለሁኝ

View Favorites