Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
ህይወቴን ከሞት ያዳነ
ስል እኔ ነፍሱን የኮነነ
የፍቅር አምላክ አለኝ
ሸክሜን የወሰደልኝ
ከአባቱ ዘንድ ተልኮ የመጣ ፍቅር
ከመከራ እኔን ነፃ ሊያወጣ ወዳጅ
ዋጋ ከፍሎ ባልሰራበት ሀጥያት
ሰው አረገኝ ኑር አለኝ በህይወት
መስቀል ተሸክሞ የተንገላታ ለኔ
በቀራኒዮ ተሰቅሎ የሞተ ህይወት
ፍቅሩ ልዩ ውድ የኔ ጌታ
ይክበር ይንገስ ሁሌም ጠዋት ማታ
ከህይወት ህይወት ለእኔ ሰጥቶኣል ግሩም
ጣልቃ ገብቶ ከሞት አድኖኛል ጀግና
የአባትነት ፍቅሩን የገለፀው
ወረት የሌለበት እውነተኛ ነው
ከሰይጣን ጋር አንድነት የለኝም ይቅር
አምልጫለው ሞት አያገኘኝም አሹ
እስራቴን ጌታዬ በጠሰ
ከብሩያለሁ ህይወቴ ታደሰ