Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
እናከብርሀለን
እናነግስሀለን
ስምህን እንባርካለን
እንገዛልሀለን
ያንን ሁሉ መከራ በአንተ አልፈነዋል
ያስለቀሰን ዛሬ ከፊታችን ጠፍቱኣል
ችግራችንን ሁሉ አሁን ረስተናል
ክበር እንልሀለን ክብር ይገባሀል
ያላሰብነው ሆኖ እኛስ ተደንቀናል
ድንቅ ተአምር ስትሰራ በአይናችን አይተናል
የሞተው ተነስቶ ለአንተ ክብር ሰጥተዋል
ተአምር ነው ድንቅ ነው ፍጥረት ያደንቁሀል
ከዛሬ ነኃላ የሚያስፈራን የለም
ሁሉ በአንተ ሆነዋል በምንም አንፈራም
የሚያሰጋን የለም አንተ ስለ አለኸኝ
ክብር እንሰጥሀለን ከሞት ስላዳንከን
ለምስጋና አባት ለተገፋው ደራሽ
ሁሌ ለሚያነባው እንባውን ከአይኑ አባሽ
ምንም በሌለበት የምትሆነው ተስፋ
እየሱስ አንተ ነህ ዘላለም ክብርህ ይስፋ