Tumim Song 63
ከጠላቴ እጅ ያዳነኝ




ከጠላቴ እጅ ያዳነኝ

Style = ----
‎Temp = ----
‎Tran = ----
‎Scale = ----
‎Cord = ----
>>>>>>

0:00
0:00



ከጠላቴ እጅ ያዳነኝ በምህረቱ
በፀናች ክንዱ የታደገኝ በጎነቱ
እንደ እግ/ር ማንም የለም
በዙፋኑ ፀንቶ የሚኖር ዘላለም

እኛን ያዳነን ከአለም መከራ
ጌታ ኤልሻዳይ ነው ሁል ጊዜ ገናና
ይገባዋል ለእርሱ ክብርና ምስጋና
የተነገረለት ዝነኛ ነውና

ጠላት መልካም መቼ አስቦ ያውቃል
ጌታ ግን መልካም ነው ህያው ሰው አድርጎዓል
ያንን ሁሉ ኃጥያት በደሙ ሽሮልን
ታማኞች አድርጎ ለአገልግሎት ሾመን

ምህረት ቸርነቱ ተከትለውናል
በለመለመ መስክ ሁሌ ይመራናል
ጠላት አይገዛንም ጌታ አስመልጦናል
በሰላም በደስታ በድል ኖረናል

ሰይጣንን ከእግሩ ስር ያንበረከከው
አልፋና ኦሜጋ እሱ ሁሉን ቻይናው
ጌታን የሚያቅተው አንዳች ነገር የለም
ብርቱ ነው እየሱስ ዛሬም ለዘላለም

View Favorites