Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
አምላኬ በአንተ ስንቱን አለፍኩኝ
ካንተ የተነሳ እኔም ሰው ሆንኩኝ
ጥበቃህ በዝቶ ለዚ ደርሻለሁ
ለወደደኝ ጌታ ምስጋናን ሰዋለሁ
ጌታዬ ውለታህ ከአይምሮ በላይ ነው
እኔን ስታድነኝ በአይኔ አይቻለሁ
ሞቴን ሞተህልኝ ጌታ ሰው አረከኝ
ለአንተ የምሰጠው ምስጋና አለኝ
ውድቀት ሽንፈት ለጠላቴ ሆኖኣል
ክብር ሞገስ ላንተ ይገባሀል
ሁሌ ደስ እያለኝ ጌታዬ ላምልክህ
ስግደትና እልልታ ላንተ ይሁንልህ
አምላኬ ስራህን ሁሌ አወራለሁ
አዳኝነትህንም እመሰክራለሁ
የሚስተካከልህ አይገኝም አቻ
ሁሌ ድንቅ አድራጊ እየሱስ ብቻ
ውለታህን ሳስብ ይጎተጉተኛል
ከቶ ዝም አትበል አመስግን ይለኛል
መሰንቆዬን ላንሳ በገናዬን ልደርድር
ይህም ያንስብሀል ለሀያሉ እግ/ር