Tumim Song 61
የወደደኝን እወደዋለሁ




የወደደኝን እወደዋለሁ

Style = ----
‎Temp = ----
‎Tran = ----
‎Scale = ----
‎Cord = ----
>>>>>>

0:00
0:00



የወደደኝን እወደዋለሁ (X2)
ማልካሙን ለእኔ አድርጎልኛል
መላ ሲጠፋ መፍትሄ ሆኖኛል
ባማረ ስራ አስቀምጦኛል
ከማንም በላይ እኔን ወዶኛል

ጠላት ሊያጠፋኝ ቢከተለኝም
ጌታ አሳልፎ ለእርሱ አይሰጠኝም
ወደ መዱን ሰብሮ አስመልጦኛል
ሰላሙን ሰጥቶ አሳርፎኛል

ላይጥለኝ እየሱሴ በእጆቼ ይዞኛል
ከሲኦል ምንጋጋ አስመልጦኛል
ጥበቃው ብዙ ነው ምህረቱ የማያልቅ
በሞት ያዳነኝ ጌታ ነው ታላቅ

ልጄ ነህ ብሎ ታል ገብቶልኛል
የእርስቱ ወራሽ አድርጎ ሾሞኛል
በህይወቴ ዘመኔ አመልከዋለሁ
ክብሬም እሱ ነው አስከብረዋለሁ

ጌታ ሆነልኝ ጋሻ መከታ
አመልከዋለሁ ሁሌ ጠዋት ማታ
ላመስግን ቆሜ ላንሳ በገና
ያደረገልኝ ብዙ ነውና

View Favorites