Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
እሱ ብቻ ነው ጌታ (X2) እሱ ብቻ
ወደር ማይገኝለት የለውም አቻ እየሱስ ብቻ
ረዳት አይፈልግም ለእጆቹ ስራ
ብቻውን ያደርጋል አስደናቂ ስራ
እኛም እረካን ከህይወት ውሃ
አሳረፈን ይሄው ከሃሩሩ ምድረ በዳ
12 አመት ደም የፈሰሳት
በሰዎች ዘንድ ከቶ ተስፋ የሌላት
ተፈወሰች እሱኣ ወደ አምላኩኣ ቀርባ
ታበሰላት ያኔ የዘመናት እንባ
38 አመት በአልጋ ተኝቶ
ተስፋ የሚያደርገውን አንዳች ነገር አጥቶ
አልጋህን ተሸክመህ እየሱስ ሂድ አለው
ታሪኩን ቀይሮ ሙሉ ሰው አረገው
ጌታ ነው ጌታዬ ጌታ ነው
አዳኝ ነው አምላኬ አዳኝ ነው
ፈዋሽ ነው እየሱሴ ፈዋሽ ነው
ወዳጅ ነው ወዳጄ ወዳጅ ነው