Tumim Song 59
ወንድሜ ቶሎ ና




ወንድሜ ቶሎ ና

Style = ----
‎Temp = ----
‎Tran = ----
‎Scale = ----
‎Cord = ----
>>>>>>

0:00
0:00



ወንድሜ ቶሎ ና
ጊዜው አልቆአልና (X2)

መንገድና እውነት ህይወት እየሱስ ነው
ታዲያ ከእርሱ በቀር በየት ልትገባ ነው
ተመለስ ወንድሜ ህይወት ይሻልሀል
የዘላለምን ሞት እርሱ ሞቶልሀል

አንተ እኮ ልጁ ነህ ሞትህን አይወድም
እንድትጠፋበት ከቶ አይፈልግም
ስላንተ ብሎ ነው ደሙን ያፈሰሰው
በቀራኒዮ መስቀል ራሱን የሰዋው

እግ/ር ቅን ፈራጅ ፈጣሪ ነውና
አንተ ብቻ ፈጥነህ ወደ እርሱ ቶሎና
የምህረት እጆቹ ዛሬም ተዘርግተዋል
ህያው ሰው ሊያደርግህ ና ልጄ ይልሀላ

እባክህ ይቅርብህ የዚ አለም ነገር
ብታውቀው ይበጅሀል የእግ/ር ሚስጥር
ፍቅር ነው ቅረበው ቅመሰው ቸርነቱን
ያኔ ትረዳለህ የአባትነት ፍቅሩን

View Favorites