Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
ጌታ ሆይ ማረን ይቅር በለን
አንተን በድለናል ባለማወቃችን (X2)
ለስጋችን ምኞት እጅጉን ሮጠናል
አንተን አሳዝነን እስካሁን ኖረናል
እባክህ ጌታ ሆይ ማረን እንደገና
በምህረትህ እየን አባብዬ ናና (X2)
እግ/ር አምላክ ቁጣህ ያስፈራል
እባክህ ማረን እንዳንሞት አደራ
ሀጥያታችን እጅግ በምድር ስለበዛ
ጌታ ሆይ ለህዝብህ ምህረትህን አብዛ
ሞታችንን ወስደህ ህይወት ሰጥተኸናል
ይህንን ዘንግተን አንተን በድለናል
በአመፃችን ብዛት ልንጠፋ ነውና
ምህረትህን አፍጥን ዛሬም እንደገና