Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
ሁሉ በአንተ ሆነ ለኔ
ክበርልኝ መድህኔ
ስላለኸኝ አባብዬ
ኖራለሁኝ ተደላድዬ (X2)
ከአንተ ወዲያ ለኔ እርካታ
የለም የሱሴ የእኔ ጌታ
እስካሁን አለሁኝ በቤትህ ፀንቼ
ከፍበል ዘላለም ተወደስ ወዳጄ
ከፍ በ ተወደስ ወዳጄ ሁሁ ሄሄ ሀሌሉያ (X3)
በይቅርታ ያልተፀፀትህ
እኔን ያየህ በምህረትህ
በቂዬ ነህ ለኑሮዬ
ክበር ንገስ አባብዬ (X2)
ውዴ አንተ ነህ የእኔ ምርጫ
ሁሌ የምትጠራኝ በቁልምጫ
አባትነትህ አርክቶኛል
ሁሌ ባንተ ደስ ይለናል (X2)
ፊትህ መቆም የቻልኩት
በአቅሜ አይደለም በእኔ ብርታት
ለውጥ የመጣው በህይወቴ
ያንተ ፀጋ ነው ደህንነቴ
ምህረትህ በዛ ለኔ
ምክንያት ሆነኝ ለመዳኔ
ተመቸኸኝ ለህይወቴ
ክበርልኝ መዳኒቴ