Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
አቤቱ አንተን በመፍራት አሳድገኝ
አምላኬ በቃልህ እውነት ምራኝ
አንተን በማወቅ አኑረኝ
ከስጋዬ ምኞት አውጣኝ
እባክህን (X2) አንተን በመፍራት አሳድገኝ
እባክህን (X2) አንተን በማወቅ አኑረኝ
የጥበብ መጀመሪያ አንተን መፍራት ነው
ክርስትና ማለት አንተን ማወቅ ነው
ግን ጌታዬ እንዳልጠፋ ይህን አውቄ
በአፍ ብቻ ሳይሆን ልወቅህ ጠንቅቄ
አንተን መፍራት ወደ ህይወት ይመራል
ላንተ መታዘዝ እስከ ፍፃሜ ያፀናል
እኔም አባቴ ሆይ ለቃልህ ልገዛ
ዘመኔ እንዳያልቅ እንዲሁ በዋዛ
ምራኝ (X2) ጌታ ሆይ ምራኝ
ምራኝ (X2) አባቴ ሆይ ምራኝ
በእውነት መንገድ ምራኝ
ከሀጥያት እንድርቅ እርዳኝ
ከአለም ምኞት እውጣኝ
ፀጋህን አልብሰኝ አፅናኝ (X2)