Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
ጌታዬ ስምህ በኔ ላይ ተጠርቶአልና
እንደቀድሞው ናና እርዳኝ እንደገና
አቤቱ የጣርህ ፍሬ ነኝ የደምህ ዋጋ ነኝ
እኔን አትተወኝ አትጣለኝ
ፊተኛ ሆኜ ዛሬ እንዳልሆን ዋለኛ
ድካም እንዳይገዛኝ ጌታ አግዘኝ
አባቴ እርዳኝ እንዳልሆን ብቸኛ
አቅምም የለኝም እኔስ ካንተ ሌላ
ሀይሌና ጉልበቴ ዝማሬዬም አንተው ነህ
ትምክቴም ኩራቴም ጋሻዬም አንተው ነህ
የሱሴ ከተውከኝ ወደማን እሄዳለሁ
ውዴ አትልቀቀኝ ፊትህ ወድቂያለሁ
ብርቱ የተባሉ በደከሙ ዘመን
የሌለውን ሳወራ የወደኩ እንዳልሆን
መንገድ ላይ እንዳልቀር በጉዞዬ ሳለሁ
እጄን በእጅህ ያዘኝ ከዳር እደርሳለሁ