Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
መድሀኒለም ክብር ይገባሀል
አንተ ቅዱስ ስግደት ይገባሀል (X2)
ከጠላት መንጋጋ ህዝብህን አድነሀላ
ከጨካኙ ከአውሬው በድንቅ ታድገሀል (X2)
ይሁንልህ ክብር ይሁንልህ አምልኮ (X2)
ድንቅን የምትሰራ አንተ አምላክ ነህና
ዛሬም ይገባሀል አዳዲስ ምስጋና
አንተ አምላክ ነህና እናመልክሀለን
ክበርን ለዘለ አለም ለአንተ እንሰጣለን (X2)
በአንተ ህይወታችን እንዲህ አምሮአልና
ቀንዳችን በጠላታችን ከፍ ብሎአልና
ጠላት ህዝብህን ሊያጠፋ
ከዋላ ሆኖ ሲያሳድድ በሰረገላ (X2)
ከፊትም ደግሞ ባህር ተዘርግቶ
ማዳንህን አይተናል በክንድህ ተመርቶ
በአምልኮ ወደ መቅደስህ እንገባለን (X2)
ምስጋናን ደርበን በፊትህ እናቀርባለን (X2)
በሽብሸባ ከዙፋንህ ስር እንሰግዳለን
በእልልታ በጭብጨባ ማደሪያህ እንገባለን