Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
ምስጋና አምልኮ
ይገባዋል ለአምላካችን
ውለታ ያደረገልን
ብሁ ነውና የአምላካችን
ቅዱስን ሁላችን የሚገባውን ክብር ለአንደኛችን
እንስጥ እንሰዋ ለውዳችን
ዝም አያሰኝም የሆነልንን ስናይ
ወይናል እኛ አዳነን እንበል የበላይ
የበላይ ነው እርሱ የበላይ (X2)
ለምንወደው ምርጫችን ለሆነው
ከገደብ በላይ ክብር ይሁንለት
ይመስገን የእኔ አባት
ማንም የማይመስለው አቤት እንዴት ልዩ ነው
ምንኛ ወደድነው በምክሩ እጅግ ግሩም ነው
በፍርዱ የማይሳሳት
አምላካችን ለቁጣ የዘገየ
ጌታ ምህረቱ ለዘላለም ነውና
ሰማይ እና ምድር ከተፈጠረ ጀምሮ
ፍጥረት ሁሉ አንተ ሊገልፅህ ሞክሮ
እስካሁን ድረስ ስለማንነትህ
አሀዱ አሉ እንጁ መች መሀል ደረሱ
አታልቅም ተገልፀህ ተገልፀህ
አትደረስም ከፍታህ አይለካም
ከዚህም ቡኃላ በሚመጣው ፍጥረት
ለዘላለም ሊነገር በሰው ሁሉ አንደበት
ስለ አንተ ጥቂቱን ነው እንዲሁ ተመስገን
ቅጥያ፡-
አልፋነህ ኦሜጋ
(ሳሙኤል ተስፋሚካኤል)