Style = ----
Temp = 83
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
እኖራለሁ ከአንተ ጋራ
ወጀብ ቢነሳ ምንም ሳልፈራ
ማበል ቢመጣ ምንም ሳልፈራ
ና ብሎ ሲጠራኝ ፍርሀት ሲሰማኝ
በማበሉ ብርታት ልቤ ተናውጦብኝ
አጠገቤ ያለው እርሱ ኤልሻዳይ
አይበገርም እርሱ ሁሉን ቻይ
ከእንግዲህ ቡኃላ የቱ ይደንቀኛል
ችግርን እንዳላይ ጌታ ሸፍኖኛል
ሁሉ ሚጠብቀኝ አምላኬ ስላለ
አልናወጥም ይሆነኛል ከለላ
የሚበልጥ እያለ ከወዳጅ ዘመድ
አምላኬ እያለ ለምን ልስደድ
ከሀዘን ገላጋይ መከራን ድል ነሺ
ስላለ ከኔ ጋር አልፈራም ጭራሽ