Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
ፈቅጃለሁ እራሴን
አስከብሬ ላልፍ እየሱሴን (X2)
ለካስ የራሴ አይደለሁም
እንዳገለግለው ተጠራሁኝ ለዘላለም (X2)
ጌታዬ የጠራኸኝ ለክብሩ ለራሱ
የከበረ ደሙን ስለኔ ማፍሰሱ
ትልቅ ዋጋ ከፍሎ እኔን የገዛኝ
እንዳገለግለው ብሎ ነው የገዛኝ
ለካስ ሳስበው ተራ ሰው አይደለሁም
የተገዛው ነኝ በጌታ በእየሱስ ደም
እኔም ለዚህ ምላሽ የሚሆነኝ
ምንም ባይኖረኝ ለክብሩ ኖራለሁኝ
ሳልወደው ወዶኝ እኔን ሊቀርበኝ
ከብዙ ሰው መሀል እኔን ላገኘኝ
ለትልቁ አላማ ለቤቱ ለሾመኝ
ምላሽ ባይሆነኝ እራሴን ሰጠሁኝ