Tumim Song 43
መቅደስ ውስጥ




መቅደስ ውስጥ

Style = ----
‎Temp = ----
‎Tran = ----
‎Scale = ----
‎Cord = ----
>>>>>>

0:00
0:00



መቅደስ ውስጥ ይግባ ምስጋናዬ (X2)
ማደሪያ ውስጥ ይግባ አምልኮዬ
ተከብረህ ተፈርተህ በዙፋንህ ላይ (X2)
ትኖራለህ ለዘለአለም ሳይገኝልህ መሳይ

ጥንትም አንተ ዛሬም አንተ እግ/ር
በታላቅ ብርሃን አሸብርቀህ የምትኖር
ታላቅ እና የተፈራህ እየሱስ ገናና
በምድር ሁሉ ላይ ታወቀ ዝና

ክበር ልበልህ ዛሬም እንደገና
ፊትህ ልቅረብ በተዋበ ዜማ
በአዳዲስ ቅኔ በአዳዲስ ዝማሬ
አስደስትሃለሁ ዝማሬን ዘምሬ

አከብርሀለው አባቴ ቀንና ማታ
ሳልታክት ሳልሰለች ሁሌ በደስታ

ገናናው እየሱስ ኦሆሆ የትንሳዬው ንጉስ
ታጅበህ ምትኖር ኦሆሆ በክብር ደመና
ተወዳዳሪ አጣሁልህ አቻቻ
መሳይ ከቶ የለህ እስከ ምድር ዳርቻ

ክበር ልበልህ ዛሬም እንደገና
ፊትህ ልቅረብ በተዋበ ዜማ
በአዳዲስ ቅኔ በአዳዲስ ዝማሬ
አስደስትሃለሁ ዝማሬን ዘምሬ

አከብርሀለው አባቴ ቀንና ማታ
ሳልታክት ሳልሰለች ሁሌ በደስታ

View Favorites