Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
በእኔ ላይ (X3) ከብረህ ታይ
በእኛ ላይ (X3) ነግሰህ ታይ
በስራህ ፃዲቅ ነህ
አቻ እኩያ የሌለህ
ጌታ ሆይ (X3)
ከብረህ ታይ (X2)
ሾሜሀለሁ በእኔነቴ
አንተው ክበር በህይወቴ
ውዴ ነህና ረዳቴ
ክበርልኝ መድሃኒቴ (X6)
የእኔ ይምለው ምንም የለም
ሁሉም እኮ የአንተ ነው
አንተ ትልቅ የእኔ ጌታ
ላክብርህ ጠዋትና ማታ
አንተ ካለ ከእኔ ጋር
በጭራሽ እኔ አልፈራም
ሰላምን ሰጥተህ ረክቻለሁ
ሁሉ በአንተ ሆነ ብዬዋለሁ (X6)
ለውለታህ ምላሽ ቢሆን
ሁሌ አንተን ልምልክህ
በህይወቴ ሁን የበላይ
ጌታ ብቻ ከብረህ ታይ (X6)