Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
አቤት እንዴት ያለ መውደድ ነው
አቤት እንዴት ያለ ፍቅር ነው
ራስራ ሚያሰዋው
ነብስን የሚያሰጠው
እንዴት ያለ መውደድ ነው
እንዴት ያለ ፍቅር ነው
ምኔን አይቶ ልበል ሕይወትን የሰጠን ጌታ
ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር አይገኝም የትም ቦታ
በቀራኒዬ መስቀል ስለ እኔ ተሰቅሎ
ነፃ አውጥቶኛል እዳዬን ከፍሎ
ባርነት ተሸሮ ነፃነቴ ታውጁኣል
ጌታ እየሱሴ መርገሜን ወስዶታል
በፈሰሰው ደሙ የራሱ አድርጎኛል
አዲሱ ፍጥረት ሆኜ እንዲህ አምሮብኛል
ሌሎች በማይችሉት ዋጋ ነው የገዛኝ
ማንም እንዳይነካኝ በምልክት ለየኝ
አንዱን ልጁን ሰጥቶ እኔን የታደገኝ
ዘመኔን በሙሉ አመልካለሁኝ