Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
እንደ እግ/ር ያለ ማንም የለምና
እርሱ ኤልሻሳይ ገናና ነውና
የተናገረውን ቃሉን ይፈፅማል
ሁሉን ማከናወን እርሱ ብቻ ያውቃል (X2)
መልካም እረኛችን ጌታ እግ/ር ነው
ዛሬም ለዘላለም ፀንቶ የሚኖረው
ጊዜ የማይሽረው ዘመን የማይሽረው
የኛ ጌታ እየሱስ እርሱ ሁሉን ቻይ ነው
ጌታችን ልዑል ነው አምሣያ የለውም
እንደ እሱ የሚሆን ማንም አይገኝም
ለቃሉ ታማኝ ነው የኛ አምላካችን
እንደ ተናገረው ይምላል ተስፋችን (X2)
እኛስ አባት አለን ፀንቶ የሚያኖረን
በምድረ በዳ ላይ መናን ሚመግበን
በእርሱ መታመን ይሻለናል
ስለ ሚሸከመን እስከ ሽምግልና (X2)
የሚያስጨንቃችሁን በኔ ጣሉት ብሎ
ያሳረፈን እርሱ ለሁሉ አስጥሎ
እረፍት ሆኖልናል ሠላም እርካታችን
የዘላለም ተስፋ እርሱ ነው ጌታችን (X2)