Tumim Song 35
መሸማቀቄ ቀረ




መሸማቀቄ ቀረ

Style = ----
‎Temp = ----
‎Tran = ----
‎Scale = ----
‎Cord = ----
>>>>>>

0:00
0:00



መሸማቀቄ ቀረ (X3)
ኑሮዬ በጌታ ሰመረ

የሰው ፊት እያየሁ እንዲያው ስሸማቀቅ
ምን ይሉኝ እያልኩ ስፈራ ስጨነቅ
አንገቴን ደፍቼ ብዙ ዘመን ኖርኩኝ
ጌታዬ ሲያየኝ ቀና ብዬ ሄድኩኝ

አንገቴን ደፍቼ ከእንግዲህ አልኖርም
ጌታ አክብሮኛል ሰው አድርጎ እኔንም
ስጋት አይገባኝም በኑሮዬ በቃ
ጌታ ገብቶልኛል በህይወቴ ጣልቃ

ተረቶ አየሁት የፈራሁት ሁሉ
ድል አጎናፀፈኝ ጌታ እንደ ቃሉ
በመከራ ደርሶ አፅንቶ አቁሞኛል
ዘምርለታለሁ እኔም ወግ ደርሶኛል

ከእንግዲህ አልሰጋም ጌታ ነው ምርኩዜ
ደግፎ የሚያቆመኝ በድካም ጊዜ
ችግር ቢሆን መከራ ከእርሱ አይለየኝም
ፀንቼ ኖራለው ከርሱ ጋር ዘላለም

በድል እወታለሁ የፈራሁትን
ይዤ ወጥቻለሁ እግ/ርን
እርሱ ይረዳኛል ለምን እሰጋለው
ጨለማዬ በርቶኣል በድል እጉኣዛለሁ

View Favorites