Style = ----
Temp = ----
Tran = +3
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
የቆምኩ እየመሰለኝ ወድቄ እንዳልገኝ
ፈልገህ ስትመጣ ቤትህ እንዳታጣኝ
በዚህ ክፉ ዘመን ጌታ እጄን ያዘኝ
ጌታ አንተው ደግፈኝ
አንተ ያየህልኝ አትኩሬ እንዳይ
የከበረውን ከተዋረደው እንድለይ
እባክህ ጌታዬ አይኔን ክፈትልኝ
የድፍረት ሀጥያቴ እኔን እንዳይገዛኝ
አስተሳሰቤን ቀይር አመለካከቴን
ጌታዬ ለውጠኝ አረ ማንነቴን
ምራኝ ወድ አባቴ በቀና መንገድ
ወድቄ እንዳልገኝ በጥፋት ግድጉኣድ
የዚህ ምድር ነገር እንዳይጎትተኝ
ወደ ፊት እድሮጥ ጌታዬ እርዳኝ
አንተ እንደምታውቀው እኔ ደካማ ነኝ
በጉዞዬ ሳለሁ እጄን በእጅህ ያዘኝ