Style = ----
Temp = ----
Tran = ----
Scale = ----
Cord = ----
>>>>>>
ምኔን አይተህ ነው እኔን የቀረብከኝ
በማያልቀው ፍቅርህ እንዲህ የወደድከኝ
አትሆነኝም ብለህ ጌታ ሳትንቀኝ
ልታፅናናኝ መጣህ ህይወት ልትሆነኝ
ጌታዬ በፊትህ እኔ ማን ነኝ
እጅግም ደካማ ሀጢያተኛ ነኝ
ነገር ግን ሀጥያቴን በመስቀልህ ሽረህ
ከዘላለም ስቃይ እኔን አወጣህ
እኔስ የገረመኝ አባዬ አጠራርህ
እኔን ደካማውን አንተ መርተህ
ጌታ ልታከብረኝ ሰው ልታደርገን
ፊትህ ልታቆመኝ ሞገስ ሰጠኸኝ
ስራዬ አይደለም እኔን የስወደደኝ
ለእኔ ያለህ ፍቅር ጌታ ግድ ስላለህ
ውለታህን እያሰብኩ ፊትህ ልስገድልህ
ስለዚህ ጌታዬ ሁል ጊዜ ላምልክህ