Tumim Song 29
ታሪክ ተቀየረ በሱ በጌታዬ




ታሪክ ተቀየረ በሱ በጌታዬ

Style = Wallo
‎Temp = 106
‎Tran = +7
‎Scale = Tizita major
‎Cord = C Major
>>>>>>

0:00
0:00



ታሪክ ተቀየረ በሱ በጌታዬ
ይኸው አምሮብኛል ሆኖኝ ወግ ማዕረጌ

እንዲህ ነው ጌታዬ (X2)
የኔ መክበሪያዬ
እንዲህ ነው ሲያከብር
ታሪክ ሲቀየር

የፈለገውን እያለ ጠላት ሲደነፋ
ጌታዬ ሆነልኝ የዘላለም ተስፋ
ውድቀትን ተመኘው የጠላቴን (X2)
በፍርድ ተዘጋጅቶ በህይወቴ
ከንቱ አደረገው መድሃኒቴ

ትሞታለህ ተስፋ በህይወት ሲቀየር
እዩኝ ይህን አምላክ አክብሮ ሲያኖር
እሱ ያውቅበታል ማኖር በከፍታ (X2)
ታሪክን ሲቀይር ድንቅ ነው ይህ ጌታ
እኔ አከብረዋለሁ ጠዋትና ማታ


ጌታዬ የጠራኝ ለውርደት አይደለም
ሊያከብረኝ እኮ ነው እስከ ዘላለም
ዘይቱን ቀባኝ በጠላት ፊት (X2)
እኔን አወጣኝ ከውርደት ሞት
እየሱስ ሆነልኝ ምቹ አባት

View Favorites