Style = Wallo
Temp = 106
Tran = +2
Scale = Tizita major
Cord = C Major
>>>>>>
እግ/ር ተነስ እነሆ ከማደሪያ
ጊዜው ያንተ ነው በኛ ላይ የመስሪያ
የኛ መሻታችን ክብርህ ነውና
ዛሬም እንላለን ናስራ (X4)
ከጥንት የነበረው ያገኘነው ክንድህ
ዛሬም ይንቀሳቀስ ይታይ ጌትነትህ
ቀንበር ይሰባበር እስራት ይፈታ
ሀይልህ ለኛ ይምጣ ሙላት በደስታ (X2)
ከቶ አይቀንስም ሙሉ ነው ስልጣንህ
ማንም አይጋራም ፅኑ አለቅነትህ
ዛሬም የአንተ ስልጣን ይታይ በዚህ ስፍራ
ለህዝብህ መጎብኘት ዛሬ ይህን ተራ
ጌታ ስትገለጥ ከላይ ከሰማይ
እኛም አይተንሀል ስትሰራ በእኛ ላይ
ጌታ ክበርልን ዛሬም ለዘላለም
አንተን የሚመስልህ ከቶ ማንም የለም