Tumim Song 26
ቱሚም የእግ/ር ክብር




ቱሚም የእግ/ር ክብር

Style = ----
‎Temp = ----
‎Tran = +5
‎Scale = Tizita major
‎Cord = C Major
>>>>>>

0:00
0:00



ቱሚም የእግ/ር ክብር የተገለጠብሽ
ቱሚም የዕርስቱ ተካፋይ እንድትሆኚ የለየሽ
ቱሚም ተነሺ እንደቃሉ ስራውን አውጂ
ቱሚም በዋሻ አይደለም ተገልጦብሸ እንጂ

እግ/ር አንቺን በእውነት መርጦሻል
በሰይጣን ግዛት ላይ አለቃ አድርጎሻል
የክብር የዜማ ጊዜ ሆኖልሻል
የሌላ አይደለሽም የኔ ነሽ ብሎሻል

በጨለማ ላሉት ብርሀን እንድትሆኚ
ክብሩን ገልጦብሻል ለእርሱ ታማኝ ሁኚ
ክብርሽን አትርሺ ተነሺ አታቅማሚ
እርሱ ሆኖልሻ ል ለህይወትሽ ተስማሚ

ቱሚምዬ ተነሽ ውድሽ ጠራሻል
ከመቼም ይልቅ ዛሬ ይፈልግሻል
አንድያ ልጁን ለአንቺ ሲል ሰቶሻል
በከበረው ደሙ የራሱ አድርጎሻል

እርሱ ልጄ ብሎ ለክብሩ አቁሞሻል
የእርስቱ ወራሽ አድርጎ ሾሞሻል
ከዘላለም ጥፋት እርሱ አስመልጦሻል
ተነሽና አክብሪው መልካም አድርጎሻል


ቅጥያ፡-
የእግ/ር ፈቃድ መገላጫ

View Favorites