Style = TVU
Temp = 104
Tran = +1
Scale = Tizita major
Cord = ----
>>>>>>
ምስጋናን ፈለገ በምህረቱ አሰበ
ያለፍኩትን መንገድ አታስነው ብሎ
የድሮ ታሪኬ በእየሱስ ተረሳ
ዛሬ ይኸው ቆምኩኝ ምስጋናን ላበዛ
የክስ ደብዳቤዎች አምሮዬን ሲሞሉ
ከጌታዬ መንገድ ሊያወጡኝ ፈለጉ
የቃሉ ባላባት የስልጣን ባለቤት
እንዲህ አለ አባባ ባላሰብኩበት ሰዓት
እርስቴ ነህ ልጄ እርስቴ ነህ መኩሪያዬ
ፍራትና ስጋት ጭንቀትም መከራ
ክፋትን ጨምሮ ጠላቴ ሲያወራ
ዝም አላሰኘውም አምላኬ ሲያየኝ
ጠላቴን ልበቀል ድብቅ ጦር ላከልኝ
እስራቴን ፈቶ ነፃ አድርጎ ሸኘኝ
ከማይረባው መንገድ ክፋት ከበዛበት
አምልጫለሁ በሱ በጌታዬ ብርታት
ከእንግዲህ ጠላቴ እኔን አታገኘኝም
ለጥርስህ ንክሻ ጌታም አልሰጠኝም
በአምላኬ ጥላ ስር አርፌ ኖራለሁ
ቅጥያ፡-
ዞር በል ጠላቴ
የማልረሳው