Style = Rock A
Temp = 104
Tran = +5
Scale = Tizita major
Cord = C major
>>>>>>
ስትረዳኝ አይቻለሁ በአይኔ
ወይኔ ዘንድሮ እንዳልሁ አልቀረሁ
ዛሬማ ሌላ ሰው ሆኛለሁ
መከራዬንም ረስቻለሁ
ሜዳና ተራራ ጋራ ሸንተራሩን
ቀና ብዬ እንዳልሄድ ያደረገኝን
ደመናውን አንስተህ ጭጋጉን ገፈኀው ከላዬ
አዜምልሀላው ይኸው ቀና ብዬ
በተገፋው መጠን ዛሬ ከብሬያለሁ
ጋሬጣዎቹንም በአንተ አልፍያለሁ
የኑሮዬ ውበት ድምቀቱ ጨምሮኣል
ሁሉ ከአንተ ለአንተ ለእኔ ሆኖልኛል
በህይወቴ ጉዳይ ስጉኣዝ በመንገዴ
ሁሉ ከኔ ጋር ማትለየኝ ጉኣዴ
በምንም አልሰጋም እርፍ ብያለሁ
ነገሬን ስትጨርስ በአይኔ አይቻለሁ
ሆዴ እያባባ ልቤን እያስከፋው
ባይተዋርነቴ ሁለ እያሳሰበው
ምን ይሻለል ብዬ ግራ ቀኝ ሳማትር
ደርሰህ አሳረፍከኝ ጌታዬ እግ/ር