Tumim Song 20
አመታትን እርሱ አሳለፈን




አመታትን እርሱ አሳለፈን

Style = ----
‎Temp = ----
‎Tran = ----
‎Scale = ----
‎Cord = ----
>>>>>>

0:00
0:00



አመታትን እርሱ አሳለፈን
ወራቶችን ቆጥሮ አደረሰን
ይመስገን ጌታችን
ይክበር አምላካችን (X2)

በሀሩሩ ግዜ ሆኖልን ከለላ
እኛን የሚረዳ የለም ከሱሌላ
ጥበቃው በዝቶልን ደርሰናል ዛሬን
እናመልክሀለን ይኸው በዝማሬ

ንጉስ ሲሾም ሲሻር የማይለወጥ
ዙፋኑ የፀና ከቶ ማይናወጥ
ዛሬም ነገም ለዘላለም እርሱ ነው ገናና
እናሳርጋለን ክብርና ምስጋና

በአመታት መሀል በድል እየመራን
በምህረቱ ብዛት ዛሬን አደረሰን
ለውለታው ምላሽ እንዳው ብሆንለት
ክበር እንበለው ሁላችን በአንድነት

በጨነቀን ጊዜ ፈጥኖ ደርሶልናል
በጌታችን ብርታት ሁሉንም አልፈናል
ታዲያ ለአምላካችን ምን ይከፈለዋል
ፍጥረት ሁሉ ይስገድ ይህም ያንስበታል

View Favorites