Tempo= ----br>
Trans= ----
Style= ----
Scale= ----
Cord= ----
>>>>>>
አንተ የኛ ጌታ መች ደክመህ ታውቃለህ
ጥንትም እንደሠራህ ዛሬም ትሰራለህ
ለአፍታ አትደክምም ክንድህ ከቶ አይዝልም
በራስህ ተማምነህ ትሰራለህ ዛሬም
ክንደ ብርቱ ሀያል ስልጣንህ ማይሻር
እንዳፈጣጠርህ ትገዛለህ ሁሉን
አምሳያ የሌለህ ጌታ ጥበበኛ
ፍጥረት ያደንቁሀል ክረምት ሆነ በጋ
ግሩም ነው ድንቅ ነው በስራህ አስደናቂ
የተነገረልህ አንተ ነህ ታወቂ
ፍጥረት ስራህን አይቶ እጅጉን ተደንቃል
እግ/ር ታላቅ ነው ብለው ያደንቁሀል
ክንድህ የበረታ ጌታ ነህ ይሉሀል
ክብርና ምስጋና ላንተ ይሰጡሀል