Tempo= ----
Trans= ----
Style= ----
Scale= ----
Cord= ----
>>>>>>
ለእኔ ያረክኝን በህይወቴ አይቻለሁና
ሁሌም እልሀለሁ እየሱስ ገናና
እደረድራለሁ መሰንቆ በገና
እሰዋልሀለሁ የአምልኮ ምስጋና
ከፍ የማደርገው አምላኮን ብቻ ነው
ደዎዬን ሁሉ ጌታ እኮ ፈዋሽ ነው
ሌላ አምላክ የለኝም እኔ የማመልከው
ከነገስታት በላይ የሆነ ጌታ ነው
ትነግረኛና ፈፅመህ አየዋለሁ
አንድም እንካን ሳይቀር እመለከታለሁ
ታማኝ አምላክ እንዳንተ አላየሁም
ጌታ ክበር ንገስ እኩያ የለህም
ከቶ የምታስፈራ በቃልህ እየፀናህ
የተነገረልህ ጌታ አንተ ብቻ ነህ
እኔ በአይኔ አየሁ ድንቅ አድርገህልኝ
ተናግረህ የማትዋሽ ጌታ ክበርልኝ
ተስፋዬ ነህ የሱስ የዘልአለም አባት
እንዳንተ የሚሆን አረ ከቶ ከየት
አይገኝም መቼም ቢፈለግ ቢፈለግ
ምስኪኑን አንስቶ ከፍ ከፍ የሚያደርግ