Tumim Song 13
በአንተ ነው ጌታዬ




በአንተ ነው ጌታዬ

Tempo= ----
Trans= ----
Style= ----
Scale= ----
Cord= ----
>>>>>>

0:00
0:00



በአንተ ነው ጌታዬ ለዚህ ያደረስከኝ
አንተ ነህ እየስሴ ለክብርህ ያቆምከኝ አሀሀ
ለውለታህ ምላሽ ሌላ ምን እላለሁ
በአደባባይ ቆሜ ስራህን ዘክራለሁ

በአለም ሳለሁኝ ጌታዬ አሰብከኝ
ልጄ አትሞትም ና ብለህ ጠራከኝ
ጠላት ሲደነፋ እጅግ ሲያስፈራራኝ
አቤቱ አምላኬ ፈጥነህ ደረስክልኝ

ባለፉት ዘመናት ግራ ተጋብቼ
የልቤን ሚረዳ ሚስጥረኛ አጥቬ
ሳነባ አይተህ ውዴ ደረስክልኝ
ወግ ምዕረግ አየሁኝ በአንተ አማረብኝ

ከእግዲህ ለአለም እኔ እጄን አልሰጥም
አንተ ከእኔ ጋር ነህ በምንም አልሰጋም
ጌታ ለአላማ ነው ከጠላት ያዳንከኝ
የራስህ አድርገህ በቤትህ የሾምከኝ

አሁንስ አበቃ የድንግዝግዝ ኑሮ
በድል እጋዛለሁ ከአሁን ጀምሮ
በፍፁም አልሰጋም ከእንግዲህ እኔ
የነፍሴ መድሐኒት ስላለህ ከጎኔ

View Favorites