Tempo= ----
Trans= +5
Style= ----
Scale= ----
Cord= ----
>>>>>>
ሁሉ በአንተ ሆነ (X2)
አስመለጥከኝ ጌታ ከጥፋት ጎዳና
ክብር ይገባሀል ክበር የኝ ጌታ
ሞገስ ይገባሀል ንገስ የእኛ አለኝታ
ሁሉን አረክና ጌታ አስደነከን
የሚመስልህ የለም የሱስ ንገስልን
ጠላት ቢደነፋ ብዙ ቢጣጣርም
በእሱ ድንፋታ ጌታ አልተበገርክም
ፈጥነህ ደረስክና ጌታችን ታደከን
ሁሉ በአንተ ሆነ ተከናወነልን
በጠላታችን ፊት ግርማ ሞገስ ሆንከን
ታሪክ ተለወጠ በአንተ አማረብን
የሞተብን ነገር ዛሬ ህይወት ዘርታል
ክበር አባታችን ያኸው ወግ አይተናል
ሌሊት በእሳት አምድ ቀኑን በደመና
ክፉ እንዳይጎዳን ጠላ ሆንከንና
ዛሬም በህይወት አለን ምንም ሳንጎዳ
አሻገርከን ጌታ ያንን ምድረበዳ
የለቅሶ የሮሮ ያ ዘመን አልፎ
ሀዘናችን ሁሉ በአንተ ተገፈፈ
ጠላት ጉድ ፈላበት በከንቱ ሲለፋ
ጌታችን ሆንክልን የዘላለም ተስፋ