Tempo= ----
Trans= ----
Style= ----
Scale= ----
Cord= ----
>>>>>>
መልካም (X4)
መልካም እረኛዬ እየሱስ አንተ ነህ
ክበር ንገስ ክበር በህይወቴ ባለውለታዬ
ክንድህ ባይደግፈኝ ፍቅርህ ባይበዛልኝ
የጠላቴን ጉልበት አንተ ባትሰብርልኝ
የእኔ እድል ፋንታ ሞት ነበር ጌታዬ
አንተ ግን አዳንከኝ የሱስ መከታዬ
ሳዝህ የደረስክልኝ አንተን መያዜ ነው
ፀንቼ መቆሜ ክንድህ ደግፎኝ ነው
የእኔ መመኪያዬ ዛሬም ቢሆን ነገም
አንተ ነህ አምላኬ በምንም አልሰጋም
ሁሉ በሁሉ ነህ ስጋት አይገባኝም
በፊትህ ለምኜ አላሳፈርከኝም
ኑሮን እኖራለሁ ክንድህ እየመራኝ
ከእጅህ እየበላሁ ምንም ሳይጎልብኝ
በምንም አልፈራም እመካብሀለው
የሚያስፈራኝ የለም አንተን ያዣለሁ
ተሸከመኸኝ እኔን እንደ አመሌ
ከጎኔ ሳትጠፋ ሳትለየኝ ሁሌ