Tumim Song 14
ተስፋ ማደርገው




ተስፋ ማደርገው

Tempo= ----
Trans= ----
Style= ----
Scale= ----
Cord= ----
>>>>>>

0:00
0:00



ተስፋ ማደርገው ጌታን ብዙ ነው
ማያሳፍረኝ አምላኬ እሱ ነው
ሌላው ይቅርብኝ ሁሉ ከንቱ ነው

ብቻዬን ስሆን ከጎኔ ይሆናል
አይዞ ልጄ አትፍራ እኔ አለሁ ይለኛል
ከእኔ ጋር ሆነህ ምን ያሰጋሀል
እኔ አለሁልህ ብዬ ያፅናናኛል

እንደ አምላኬ የቅርቤ ጋደኛ
የውስቴን የሚያውቅልኝ ልዩ ሚስጥረኛ
ሀሳቤ ቢከፋው ተመለስ ሚለኝ
እኔስ የሚመቸኝ መካሪ አባት አለኝ

ሌላው ይቅርብህ እኔ እሻላለሁ
የእርስቴ ወራሽ አድርጌ ሾሜሀለሁ
እያለኝ ሁሌ ሁሌ ያፅናናኛል
ከእናት ከአባትም ይበልጥብኛል

የገባሁልህን ቃል እፈፅማለሁ
አንተ ለእኔ ኑር ሁሉን አደርጋለሁ
እያለኝ ጌታ ሁሌ ይመክረኛል
እንደ እርሱ ያለ አባት ከወዴት ይገኛል

View Favorites