Tumim Song 12
እየሱስ ለእኔስ ሆንክልኝ




እየሱስ ለእኔስ ሆንክልኝ

Tempo= ----
Trans= ----
Style= ----
Scale= ----
Cord= ----
>>>>>>

0:00
0:00



እየሱስ ለእኔስ ሆንክልኝ መሸሸጊያ ዋሻ
ለክብርህ አቆምከኝ ሆንክልኝ መሸሻ

ጠላቴ ሊያጠፋኝ ብዙ ጥሮ ነበር
አለሁ እስከ ዛሬ ስትረዳኝ እግ/ር
አፋን ለከፈተ ለጠላት ሳትሰጠኝ
አደረስከኝ ዛሬን በድል ስትመራኝ

ምን ልብልህ እኔ ለውለታህ ጌታ
ለክብርህ አቆምከኝ እኔን በከፍታ
ያረክልኝ ብዙ ከአይምሮ በላይ ነው
ልስገድልህ ልገዛልህ ይህም ሲያንስብህ ነው

ከፍ በል ልበልህ ሁሌ ጠዋት ማታ
ከጠላት አዳንከኝ ሆነኸኝ መከታ
አረ ግነንልኝ አንተ ድንቅ አምላክ
ሁሉን በስልጣንህ ምታንበረክክ

ጌታ የአንተ ስራ መች ያልቃል ተቆጥሮ
ይመቻል ይደላል ከአንተ ጋር ኑሮ
ከቤትህ አልወጣም ተመችተከኛል
አንተ ገብተህ ቤቴ ዛሬ አምሮብኛል

ቃላት አጣሁልህ ስላንተ ላወራ
ያደረክልኝን ሁሉንም በተራ
ልዩ ነህ አምላኬ የሚመስልህ የለም
ፍጥረት ይስገድልህ ዛሬም ለዘላለም


ቅጥያ፡-
ክብሩ ሰማያትን ሸፍኖዓል
ዞር በል አንተ ክፉ
ዋአ ኢኮቶ ኢና

View Favorites