Tempo= ----
Trans= ----
Style= ----
Scale= ----
Cord= ----
>>>>>>
ንጉስ ነህ አቻ ተወዳዳሪ የማይገኝልህ
ሀያል ነህ የሚስተካከልህ በፍፁም የሌለህ
ካንተ ሌለ ለኛ የሚበጀን
የለምና እኛን ሚሸከመን
ከሰማነው ካየነው በላይ
ጌታ እንተ ነህ ከሁሉ የበላይ
አቻ የለህ የአለም ሁሉ ንጉስ
ዝነኛ ነህ የእኛ ጌታ እየሱስ
አንጨርስም ስራህን ዘምረን
አዶናይ ነህ ሁሌም ንገስልን
ፃዲቅ ፈራጅ እንደ እንተ ማነው
ፍርድህ ሁሌ ሁሌም ትክክል ነው
በአምባው ላይ ሆነህ ትፈርዳለህ
እውነትኛ ጌታ እንተ ብቻ ነህ
አይተንሀል ስትሰራ በአይናችን
ትመቻለህ ግዛን አባታችን
እየሱስ ልዩ የሚመስልህ የለም
ክበር ንገስ ዛሬም ለዘላለም