Tempo= ----
Trans= ----
Style= ----
Scale= ----
Cord= ----
>>>>>>
ክበር ያከበርከኝ (X2)
ያንተው ያደረከኝ (X2)
አናት ነህ እኮ
ለዳት ነህ እኮ
ይብቃት አልከኝ የአለም ኑሮ
የእኔ ነህ አልከኝ ከአሁን ጀምሮ
ምላሽ የለኝም ለውለታህ
ሌላ ምን ልበል ላመስግንህ
የኔን መከራ የሚረዳኝ ጠፍቶ
ዲያቢሎስ ሲያጋራ ሊውጠኝ ተነስቶ
አበቃልኝ ብዬ እንባዬን ሳነባ
ፈጥነህ ደረስክና ታደከኝ አባባ
ውለታህ በዛልኝ ጌታዬ ለእኔ
ብዙ አደረክልኝ በህይወት ዘመኔ
ብቆጥረው አያልቅም ከአይምሮ በላይ ነው
ክበርልኝ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ
መታመኛዬ ነህ ለእኔስ መድሀኒቴ
ጋሻዬ እንተ ነህ ክበር ውድ አባቴ
ከቤትህ አልወጣም ተመችተኸኛል
ግዛኝ ለዘላለም መገዛት አምሮኛል