Tumim Song 8
ኤልሻዳይ ነው ጌታ




ኤልሻዳይ ነው ጌታ

Tempo= ----
Trans= +3
Style= ----
Scale= Tizita Major
Cord= C Major
>>>>>>

0:00
0:00



ኤልሻዳይ ነው ጌታ እልሻዳይ
ኤልሻዳይ ነው እየሱስ እልሻዳይ
የዘመናት ንጉስ የአለም ሁሉ ጌታ
እሱ ነው ጌታዬ ሁሌም የእኔ አለኝታ

ጌታ ለታመነው ያቆማል በከፍታ
የሚሳነው የለም እየሱስ የኔ አለኝታ
ለምድራዊ ኑሮ ለሚጠፋው ነገር
አልቅበዘበዝም ይዣለሁ ጌታዬን

በትንሽ በትልቅ መቼ ይለወጣል
ወንበሩ እንደ ፀና ተከብሮ ይኖራል
በአይምሮ ስፋት ከቶ አይገመትም
በሰው እውቀት ጌታ አይገመትምም

ሰው ደረስኩ ብሎ ከሚያውቀው በላይ
እውቅናን ያገኝ በምድር በሰማይ
አረ እንደርሱ ያለ የሚሆን ኤልሻዳይ
አላየሁም እኔ ጌታ ነው የበላይ

በነበረው ዘመን በሚመጣውም
ግርማዊነትህ ያለው አላገኘሁም
እሱን በሾምኩ ቀን በህይወቴ ላይ
በልጦ አገኘሁት ሆኖ የበላይ


ቅጥያ፡-
ታሪኬን
ውርደቴን

View Favorites