Tempo= ----
Trans= +3
Style= ----
Scale= Tizita Major
Cord= C Major
>>>>>>
ሀ ሀሌሉያ (X4)
የእኛ ጌታ የለህ እኩያ ሀሌሉያ
የእኛ እየሱስ የለህ አምሳያ ሀሌሉያ
አንተ በሰጠከኝ ባለን ዘመን
እናመልክሀለን አምላካችን
ክበር እንላለን ፊትህ ወድቀን
ማደሪያህን ይሙላው ምስጋናችን
ማን ብለን ሰይመን እንጥራህ
ከመታወቅ አልፋል ውለታህ
አፋችንን ሞልተን ምንዘምረው
በእኛ የሰራከው አስገርሞን ነው
ክበር እንላለን አምላካችን
ይህ ነው የምንሰጥህ መስዋታችን
አምሳያ የለህም ንጉሳችን
መቅደስህን ይሙላው ዝማሬያችን
ውለታ ሚያስገርም የእኛ ጌታ
ለምስኪኖች ደራሽ ጠዋት ማታ
በምንም በማንም ማትረታ
ዙፋንህ ፅኑ ነው የእኛ አለኝታ