Tempo= ----
Trans= +4
Style= ----
Scale= Bati
Cord= D Natural
>>>>>>
አንተ ብቻ ጌታ እረዳት የሌለህ
አንተ ብቻ ጌታ አምሳያ የሌለህ
በዙፋንህ ነግሰህ ከብረህ የምትታይ
አንተ ብቻ ጀግና ከሁሉ የበላይ
ጌታ ነህ እየሱስ ጌታ ነህ
ሀያል ነህ እየሱስ ሀያል ነህ
የሁሉ የበላይ
የሱሴ ክብርህን አረ ማን ይጠግባል
ባንተ የታመነ በምንስ ይከፋል
በሰላም በደስታ ተማምኖ ይኖራል
ጌታ እኮ ልዩ ነህ ማንስ ይመስልሀል
አንተን ሊቃወሙ ብዙዎች ተነሱ
ከቶ ግን አልቻሉም ስራህን ሊያፈርሱ
የሚገዳደርህ ጌታ ማንም የለም
በጠቢባን ጥበብ አንተ አትገመትም
እንደ አንተ ያለ ዙፋኑ የፀና
ክብሩ የሚያስፈራ የሆነ ገናና
አይገኝም ከቶ ቢፈለግ ዘላለም
ጌታችን ገዢነህ የሚመስልህ የለም
ጌታ እየሱስ ትልቅ ሁሉን ገዢ አምላክ
ሳይቀርቡህ የምትቀርብ ግርማህ
አንተን የሚመስል አንዳች አልተገኘም
አይገኝም ደግሞም እስከ ዘላዓለም